Tuesday, June 2, 2015
Dawro Culture
ዳውሮ ጎራ ብንልም ስላልተወራለት መስህብ ብቻ እናወራለን። በእርግጥ የዳውሮ ጥንታዊ ቤተ መንግስት /ካቲ ጋዱዋ/ ውበቱም ህይወቱም አልተወራም። አንበሳን ጨምሮ በዱር እንስሳትና በውብ ደን የታጀበው የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ብዙ ባይባልለትም ዛሬ ግን
የቻይናውን ግንብ የመሰለው ይህ ግንብ እንዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ ኖሯል ቢባል ለሰሚው ግራ ነው። ይህችን ሀገር የማያውቁ ግና የሚያውቋት የሚስላቸው ሊከራከሩ፣ የለም ብለውም ሊወራረዱ ይችላል። የሚያሳምነው ረጅም ግንብ ዛሬም ቆሟልና ሳንተዛዘብ መተማመን እንችላለን። ለመተማመን ደግሞ እነሆ ከአምስት መቶ ዓመት በላይ እድሜን ያስቆጠረው ካብ አንድ ዙር ርዝመት 170 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝመውን ሀላላ ካብ እንተርከው። ከዚያ በፊት አይናችሁን ጨፍኑና ርዝመቱን አስቡት የጎፋ፣ የወላይታን፣ የካፋንና የጅማን ድንበር በሙሉ ያካልላል። የእኛውና ዳውሮ ያለው ሀላላ ካብ፤
የድንጋዩ ካብ ስራ ከ1582 እስከ 1607 ባለው ጊዜ የተሰራ ሲሆን በተለይም በወላይታ በከምባታና በጎፋ ወሰን ያለው ግዙፍ እና ረዥሙ ካብ ከኤሌ እስከ ዛባ ጋራባ የተዘረጋው ነው። ይህ ግንብ ከሁለት ሜትር ተኩል እስከ ሶስት ሜትር የሚደርስ ቁመት ሲኖረው ከሁለት ሜትር ተኩል በላይ የጎን ስፋት አለው። ይህ የዳውሮዎች ታሪካዊ ቅርስ ለታላቋ ኢትዮጵያ አንድ የኩራት ምንጭ ነው። ይህ ታሪክ አያሌ ድንቅ ታሪካዊ ቅርሶችን መፍጠር ችሏል።
Edigetu-UoG-2006twitter
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment