Monday, June 1, 2015

Dawro

        ወደ ዳውሮ ጎራ ያላችሁ የተፈጥሮ መስህብ አድናቂዎች ድንገት ኩራንቶ ፏፏቴን ተመልክታችሁ ስለዚህ ሳንሰማ ቀረን ብትሉም በእርግጥ ምንም አልተወራለትም። ግን ቀጥለናል። ስለ አንዱ መስህብ ስለ ሀላላ ካብ ትንሽ ልበል።
Bala yoyo-photo by Edigetu-2006
ዳውሮ ጎራ ብንልም ስላልተወራለት መስህብ ብቻ እናወራለን። በእርግጥ የዳውሮ ጥንታዊ ቤተ መንግስት /ካቲ ጋዱዋ/ ውበቱም ህይወቱም አልተወራም። አንበሳን ጨምሮ በዱር እንስሳትና በውብ ደን የታጀበው የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ብዙ ባይባልለትም ዛሬ ግን
የቻይናውን ግንብ የመሰለው ይህ ግንብ እንዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ ኖሯል ቢባል ለሰሚው ግራ ነው። ይህችን ሀገር የማያውቁ ግና የሚያውቋት የሚስላቸው ሊከራከሩ፣ የለም ብለውም ሊወራረዱ ይችላል። የሚያሳምነው ረጅም ግንብ ዛሬም ቆሟልና ሳንተዛዘብ መተማመን እንችላለን። ለመተማመን ደግሞ እነሆ ከአምስት መቶ ዓመት በላይ እድሜን ያስቆጠረው ካብ አንድ ዙር ርዝመት 170 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝመውን ሀላላ ካብ እንተርከው። ከዚያ በፊት አይናችሁን ጨፍኑና ርዝመቱን አስቡት የጎፋ፣ የወላይታን፣ የካፋንና የጅማን ድንበር በሙሉ ያካልላል። የእኛውና ዳውሮ ያለው ሀላላ ካብ፤
የድንጋዩ ካብ ስራ ከ1582 እስከ 1607 ባለው ጊዜ የተሰራ ሲሆን በተለይም በወላይታ በከምባታና በጎፋ ወሰን ያለው ግዙፍ እና ረዥሙ ካብ ከኤሌ እስከ ዛባ ጋራባ የተዘረጋው ነው። ይህ ግንብ ከሁለት ሜትር ተኩል እስከ ሶስት ሜትር የሚደርስ ቁመት ሲኖረው ከሁለት ሜትር ተኩል በላይ የጎን ስፋት አለው። ይህ የዳውሮዎች ታሪካዊ ቅርስ ለታላቋ ኢትዮጵያ አንድ የኩራት ምንጭ ነው። ይህ ታሪክ አያሌ ድንቅ ታሪካዊ ቅርሶችን መፍጠር ችሏል።
የዳውሮ ካውካ ስርወ መንግስት በዳውሮ የአስተዳደር ስርዓት የጎላ ታሪክ የሚይዝ ነው። ከዳውሮዎች የታሪክ ድርሳን ስማቸው ደምቆ የተጻፈው ንጉስ ሀላላ በኢትዮጵያ መሪዎች ታሪክ ለትውልድ ቅርስ ትተው ካለፉ የኩራት አብነቶች አንዱ ናቸው። ንጉስ ሀላላ ስልጣንን በግል ጠቅልሎ ከመያዝ ልማድ በመውጣት አያሌ አዳዲስ የአመራር ስልቶችን ማሳየት የቻሉ መሪ ነበሩ። በተለይም ስልጣንን ለህዝብ በማካፈልና በየደረጃው በማውረድ ህዝባዊ አገዛዝን መመስረቱ ላይ የተዋጣላቸው እንደሆኑ የህዝብ አንድነትን እንደሚጠይቁ የሚያሳዩት የታሪክ ቅርሶች ምስክሮች ናቸው።
ጦረኛነታቸውም ቢሆን ድል አድራጊነትን የተሞላ እንደነበር የሚነገርላቸው ንጉስ ሀላላ የዳውሮን ድንበር ከልሎ በማጠር አልፎም በማስከበር ስኬታማ የአስተዳደር ዘመን አስቆጥረዋል። ዛሬ በኦሞ ወንዝ ተፋሰስ ዙሪያ ተገትሮ ታሪክ የሚመሰክረው የንጉስ ሀላላ ካብ ለዚሁ የዳውሮን ቅጥር ለማስከበርና ለጠላት መከላከያነት የተከተረ ነው።
የሀላላ ካብ ከካቡ ውጭ የሚመጣውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና ለመከላከል እንዲያስችል ሰባት በሮች ተበጅተውለታል። በሮቹ የየራሳቸው መጠሪያ ስም እና መገለጫ አላቸው። እነዚህም በሮች በየኤላ የከፋ በር፣ የቁጫና የጎፋ በር፣ የዚማ ወላይታ በር፣ የዩሊማሎ በር፣ የዛባ ጋራዳ የቦምቤ በር፣ የአባ የጂማ በር ይባላሉ።
ድንጋይ በድንጋይ ላይ በማነባበር ግዙፍ አለቶችን በታትኖ ይህንን መሰል አንዳች ያልተወራለት ረዥም ግንብ በመገንባት ለታሪክ ማኖር የቻሉት ቀደምት የዳውሮ ነገስታት ጥለውት ያለፉት ቅርስ ወደ ገንዘብ ሊቀየር ሊጎበኝና የውጪ ምንዛሪን ልናፍስበት የሚያስችል የቱሪዝም ሃብት ነው።
በተለይም ቅርሱ በድንቁ ዲንኬ የሙዚቃ መሳሪያ እያጫወቱ እንግዳን ማስተናገድ በሚችሉት የዳውሮ ህዝቦች ማዕከል መገኘቱ ጎብኚ የበለጠ በቆይታው እንዲደሰት የሚያደርግ ነው። እግረ መንገድ አስደናቂውን የጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክንም ለመጎብኘት ምቹ ነው። ያኔ ስለ ረዥሙ የቻይና ግንብ ሲወራ ስለ ሀላላ ካብ ለማውራት አቅም ይኖረናል። ስለ ሀገራችን የማናወራው ሀገራችን ምንም ስለሌላት ሳይሆን ሀገራችንን ምንም ስለማናውቃት ነው። ሀላላ ካብ በካብነቱ ቢረዝምም ሀገራችንን የማወቅ ባህላችን የተዳፈነ ረጅም ዘመን እንደኖረም ይነግረናል። የሚነግረን እውነት እንዳንክደው እንኳን ማየት ሳንሰማው የኖርንው የሀላላ ካብ አጥር ሆኖበታል። በእርግጥም ሀላላ እስከዛሬ ቦታው ላይ ከነበረ እኛ የት ነበርን?
ዳውሮ ጎራ ብንልም ስላልተወራለት መስህብ ብቻ እናወራለን። በእርግጥ የዳውሮ ጥንታዊ ቤተ መንግስት /ካቲ ጋዱዋ/ ውበቱም ህይወቱም አልተወራም። አንበሳን ጨምሮ በዱር እንስሳትና በውብ ደን የታጀበው የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ብዙ ባይባልለትም ዛሬ ግን ምንም አንልለትም። ወደ ዳውሮ ጎራ ያላችሁ የተፈጥሮ መስህብ አድናቂዎች ድንገት ኩራንቶ ፏፏቴን ተመልክታችሁ ስለዚህ ሳንሰማ ቀረን ብትሉም በእርግጥ ምንም አልተወራለትም። ግን ቀጥለናል። ስለ አንዱ መስህብ ስለ ሀላላ ካብ ትንሽ ልበል።
የቻይናውን ግንብ የመሰለው ይህ ግንብ እንዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ ኖሯል ቢባል ለሰሚው ግራ ነው። ይህችን ሀገር የማያውቁ ግና የሚያውቋት የሚስላቸው ሊከራከሩ፣ የለም ብለውም ሊወራረዱ ይችላል። የሚያሳምነው ረጅም ግንብ ዛሬም ቆሟልና ሳንተዛዘብ መተማመን እንችላለን። ለመተማመን ደግሞ እነሆ ከአምስት መቶ ዓመት በላይ እድሜን ያስቆጠረው ካብ አንድ ዙር ርዝመት 170 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝመውን ሀላላ ካብ እንተርከው። ከዚያ በፊት አይናችሁን ጨፍኑና ርዝመቱን አስቡት የጎፋ፣ የወላይታን፣ የካፋንና የጅማን ድንበር በሙሉ ያካልላል። የእኛውና ዳውሮ ያለው ሀላላ ካብ፤
የድንጋዩ ካብ ስራ ከ1582 እስከ 1607 ባለው ጊዜ የተሰራ ሲሆን በተለይም በወላይታ በከምባታና በጎፋ ወሰን ያለው ግዙፍ እና ረዥሙ ካብ ከኤሌ እስከ ዛባ ጋራባ የተዘረጋው ነው። ይህ ግንብ ከሁለት ሜትር ተኩል እስከ ሶስት ሜትር የሚደርስ ቁመት ሲኖረው ከሁለት ሜትር ተኩል በላይ የጎን ስፋት አለው። ይህ የዳውሮዎች ታሪካዊ ቅርስ ለታላቋ ኢትዮጵያ አንድ የኩራት ምንጭ ነው። ይህ ታሪክ አያሌ ድንቅ ታሪካዊ ቅርሶችን መፍጠር ችሏል።
የዳውሮ ካውካ ስርወ መንግስት በዳውሮ የአስተዳደር ስርዓት የጎላ ታሪክ የሚይዝ ነው። ከዳውሮዎች የታሪክ ድርሳን ስማቸው ደምቆ የተጻፈው ንጉስ ሀላላ በኢትዮጵያ መሪዎች ታሪክ ለትውልድ ቅርስ ትተው ካለፉ የኩራት አብነቶች አንዱ ናቸው። ንጉስ ሀላላ ስልጣንን በግል ጠቅልሎ ከመያዝ ልማድ በመውጣት አያሌ አዳዲስ የአመራር ስልቶችን ማሳየት የቻሉ መሪ ነበሩ። በተለይም ስልጣንን ለህዝብ በማካፈልና በየደረጃው በማውረድ ህዝባዊ አገዛዝን መመስረቱ ላይ የተዋጣላቸው እንደሆኑ የህዝብ አንድነትን እንደሚጠይቁ የሚያሳዩት የታሪክ ቅርሶች ምስክሮች ናቸው።
ጦረኛነታቸውም ቢሆን ድል አድራጊነትን የተሞላ እንደነበር የሚነገርላቸው ንጉስ ሀላላ የዳውሮን ድንበር ከልሎ በማጠር አልፎም በማስከበር ስኬታማ የአስተዳደር ዘመን አስቆጥረዋል። ዛሬ በኦሞ ወንዝ ተፋሰስ ዙሪያ ተገትሮ ታሪክ የሚመሰክረው የንጉስ ሀላላ ካብ ለዚሁ የዳውሮን ቅጥር ለማስከበርና ለጠላት መከላከያነት የተከተረ ነው።
የሀላላ ካብ ከካቡ ውጭ የሚመጣውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና ለመከላከል እንዲያስችል ሰባት በሮች ተበጅተውለታል። በሮቹ የየራሳቸው መጠሪያ ስም እና መገለጫ አላቸው። እነዚህም በሮች በየኤላ የከፋ በር፣ የቁጫና የጎፋ በር፣ የዚማ ወላይታ በር፣ የዩሊማሎ በር፣ የዛባ ጋራዳ የቦምቤ በር፣ የአባ የጂማ በር ይባላሉ።
ድንጋይ በድንጋይ ላይ በማነባበር ግዙፍ አለቶችን በታትኖ ይህንን መሰል አንዳች ያልተወራለት ረዥም ግንብ በመገንባት ለታሪክ ማኖር የቻሉት ቀደምት የዳውሮ ነገስታት ጥለውት ያለፉት ቅርስ ወደ ገንዘብ ሊቀየር ሊጎበኝና የውጪ ምንዛሪን ልናፍስበት የሚያስችል የቱሪዝም ሃብት ነው።
በተለይም ቅርሱ በድንቁ ዲንኬ የሙዚቃ መሳሪያ እያጫወቱ እንግዳን ማስተናገድ በሚችሉት የዳውሮ ህዝቦች ማዕከል መገኘቱ ጎብኚ የበለጠ በቆይታው እንዲደሰት የሚያደርግ ነው። እግረ መንገድ አስደናቂውን የጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክንም ለመጎብኘት ምቹ ነው። ያኔ ስለ ረዥሙ የቻይና ግንብ ሲወራ ስለ ሀላላ ካብ ለማውራት አቅም ይኖረናል። ስለ ሀገራችን የማናወራው ሀገራችን ምንም ስለሌላት ሳይሆን ሀገራችንን ምንም ስለማናውቃት ነው። ሀላላ ካብ በካብነቱ ቢረዝምም ሀገራችንን የማወቅ ባህላችን የተዳፈነ ረጅም ዘመን እንደኖረም ይነግረናል። የሚነግረን እውነት እንዳንክደው እንኳን ማየት ሳንሰማው የኖርንው የሀላላ ካብ አጥር ሆኖበታል። በእርግጥም ሀላላ እስከዛሬ ቦታው ላይ ከነበረ እኛ የት ነበርን? Edigetu-UoG.

1 comment: